Librería Samer Atenea
Librería Aciertas (Toledo)
Kálamo Books
Librería Perelló (Valencia)
Librería Elías (Asturias)
Donde los libros
Librería Kolima (Madrid)
Librería Proteo (Málaga)
በዚህ መጽሐፍ ልሙድ ሥነ-እንቅስቃሴን ወይም ኒውተናዊ ሥነ-እንቅስቃሴ የሚባለውን ቀንጭበን እንመለከታለን። መጽሐፉ አራት ምዕራፎች አሉት። በመጀመሪያው ምዕራፍ በቦታ እና በጊዜ ላይ በተለያዩ አሳብያን የተደረጉ ሐተታዎች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምዕራፍ እስከ ኒውተን ዘመን የነበረውን ሐተታ እንቅስቃሴ ባጭሩ ቀርቧል ፣ ምዕራፉ የኒውተንን ሦስት መሰረታዊ የእንቅስቃሴ ሕግጋት ድንጋጌዎችን በማቅረብ ይቋጫል። ምዕራፍ ሦስት የልሙድ ሥነ እንቅስቃሴን ሒሳባዊ ሐተታ ያቀርባል ፤ በምዕራፉ አስፈላጊ ብይኖች ፣ የእንቅስቃሴ ዐይነቶች እና ሒሳባዊ ስሌቶቻቸው ባጭሩ ቀርበዋል። የመጨረሻው ምዕራፍ የኒውተንን የእንቅስቃሴ ሕግጋት በአመች ቅርጽ ለማስቀመጥ ከኒውተን በኋላ የተበለጸጉትን ላግራኝዣዊ እና ሐሚልተናዊ አቀራረቦችን ውልብታ ይዟል። መልካም ንባብ።