Rev. Dr. Don L. Davis / RevDrDon LDavis
የክርስቲያን ሚሽን መሰረቶችየሚሽን/ተልእኮ ጽንሰ ሃሳብ በከተማ አብያተ ክርስቲያኖቻችን ዘንድ ሊኖረው የሚገባውን ያህል ትኩረት ሲያገኝአንመለከትም፡፡ ከውቅያኖስ ማዶ ተሻግሮ በሁሉም የዓለም ማዕዘናት ውስጥ እንዳለ ሥራ በስፋት ከተመለከትነው ፣ለሚሽን የሚገባውን ዓይነት ትንታኔ ለመስጠት አለመቻላችንን እንረዳለን ፡፡ በአንድ በኩል የክርስትና እምነት በጥቅሉእንደ ተልእኮው ምላሽ ተደርጎ ሊታይ ይችላል፣ ይህም ምላሽ ወደ አሕዛብ ሄዶ የናዝሬቱ የኢየሱስን የእግዚአብሔርመንግሥት ጌትነት እና ንግስና ለማወጅ የተደረገው ጥሪ ምላሽ ተደርጎ ሊታይ ይችላል ፡፡ አዲስ ኪዳን በክርስትናእምነት ውስጥ ፈር ቀዳጅና ዋና ሚስዮናውያን በነበሩ ሐዋርያት ለተመሰረቱት አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠ የሚስዮናዊሰነዶች ስብስብ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በክርስቶስ በኩል ወደ ዓለም በመምጣትና ዓለምን ከራሱ ጋር በማስታረቅየመጀመሪያው ሚስዮናዊ ነው (2 ቆሮ. 5፥18-21)፤ በእርግጥም ክርስትና ተልእኮ ነው ፡፡በመሆኑም በዚህ ሞጁል ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር የሚሽንን ሥነ-መለኮት ለመረዳት ሚሽንን እንደ ትእይንት ፣ሚሽንን እንደ ፍቅር እና ጦርነት በተለያዩ መነጽሮች እንቃኛለን ፡፡ በእነዚህም መነጽሮች እይታ ሚሽን በታሪክ ውስጥእና በየዘመናቱ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ለሰው ልጆች ቤዛነትን ለማምጣት የተጠቀመበት መሳሪያ መሆኑንከቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቀስ እንመለከታለን።በተጨማሪም በተለይ ለከተማ ሚሽን በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሁለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጉዳዮች እንመለከታለን።ከመጀመሪያው ጀምሮ ፣ የእግዚአብሔር ፍትሕ በከተማው ውስጥ ነግሶ እና ድህነት ተወግዶ በጽድቅ ይተካ ዘንድ ለጌታቃል ኪዳን እንዲህ ባለው ታማኝነት ውስጥ እንዲኖሩ እግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ማህበረሰብ ሾሟል።