LIBROS DEL AUTOR: ermias tilahun

4 resultados para LIBROS DEL AUTOR: ermias tilahun

  • መመለስና መታደስ
    Ermias Tilahun / ኤርምያስ ጥላሁን
    አሁን ባለንበት ዘመን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመድረስ ጂ.ፒ.ኤስ (GPS) እንጠቀማለን። ጂ.ፒ.ኤስ ሳተላይትን የሚጠቀም ቴክኖሎጂ ሲሆን፣ ከአንድ መልክዓ ምድር ወደ ሌላ መልክዓ ምድር ለመድረስ ተመራጭና አቋራጭ መንገዶችን እየመራ የሚያደርስ ነው። መንፈሳዊ ሕይወታችንም ወደ መዳረሻው ማምራት ያለበት የጉዞ እንቅስቃሴ ነው። የምንሄድበትን መዳረሻ ካላወቅን፣ ጂ.ፒ.ኤስ ልንጠቀም አንችልም። ጂ.ፒ.ኤስ ጥቅም የሚሰጠን መዳረሻችንን ካወቅን ነው። መዳረሻችንን ካላወቅን፣ ጂ.ፒ.ኤስ ሊመራን አይችልም። ስለዚህ፣ ጂ.ፒ.ኤስ ስንጠቀም ሦስት ቦታዎች አሉ፦ ያለንበት፣ የምናልፍበትና የምንደርስበት።ይህ መጽሐፍ...
    Disponible

    7,16 €

  • Jehovah Nessi
    Ermias Tilahun
    ያህዌ ንሲ - በዓላማ መኖርሰዎች ለባንዲራዬ እሞታለሁ ሲሉ፣ ለጨርቁ ማለታቸው አይደለም፤ በዚያ ሰንደቅ ለተወከለው ታሪክ፣ እሴት፣ ባህል፣ ግዛት (territory)ና ዓላማ ማለታቸው ነው። በዚያ ባንዲራ ውስጥ ብዙ ነገር ያያሉ። ከራሳቸው የሚሰፋና የሚተልቅ ነገር ያያሉ። ሙሴ እንደ ሰንደቅ ዓላማ በትሩን ከፍ ካደረገ በኋላና አማሌቅን ካሸነፈ በኋላ እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው ('ያህዌ ንሲ') የሚል መሠዊያ ሠራ። ለእግዚአብሔር ሕዝብ የድል መሠረት የሆነውን ነገር በዚህ መሠዊያ አሠመረበት። ከግብጽ የወጡ እስራኤላውያን ከራሳቸው የሚሰፋና የሚበልጥ ነገር ማየት ካልቻሉ፣ እግዚአብሔር ወዳሰበው ነገር ለመድረ...
    Disponible

    8,60 €

  • የመንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ
    Ermias Tilahun
    መንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ ነው፤ ከአንድ የአመለካከት፣ የሕይወት፣ የባሕሪ፣ የአቅም፣ የብስለት የራእይ ደረጃ ወደ ሌላ የአመለካከት፣ የሕይወት፣ የባሕሪ፣ የአቅም፣ የብስለትና የራእይ ደረጃ የሚደረግ ጉዞ። ለዚህ ዓይነቱ ጉዞ ቀጥተኛ ምሳሌ እንዲሆነን እግዚአብሔር ዘጸአት የተባለ የዕብራውያንን የጉዞ ዘገባ የያዘ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲቀመጥልን አድርጓል። በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ውስጥ ከሌለን፣ ሕይወታችን ወደ ሃይማኖታዊነት ያሽቆለቁላል። ሕያው የሆነ የክርስትና ሕይወት ይዘት እንዳለን የሚታወቀው በምናደርገው የወደፊት ተራማጅ ግስጋሴ ነው። ጉዞ ካለ እንቅስቃሴ፣ እርምጃ፣ መሻሻል፣ እድገት፣ ተጽዕኖ...
    Disponible

    12,47 €

  • ከድህነት መውጫ መሰላሎች
    Ermias Tilahun
    ድህነት የገንዘብ እጥረት ሳይሆን አስተሳሰብ ነው። ብዙ ገንዘብ ኖሯቸው ከድህነት ግን ያልተላቀቁ ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚህ ምንም እንኳን የገንዘብ እጥረት ባይኖርባቸውም፣ አስተሳሰባቸው ውስጥ ያለው ድህነት ስላልተሸነፈ፣ ይህ፣ ድህነት ከሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት፣ በባህሪያቸው፣ በስብዕናቸው፣ በተለያየ መልኩ ይገለጣል። ስለዚህ፣ ድህነት የገንዘብ ድህነት ብቻ ሳይሆን፣ የባህሪ ድህነት፣ የአስተሳሰብ ድህነት፣ የስብዕና ድህነት፣ የግንኙነት ድህነት፣ የባህል ድህነት ወ.ዘ.ተ ተብሎ ሊዘረዘር ይችላል። ከእነዚህ ሁሉ ግን፣ መሰረታዊው የአስተሳሰብ ድህነት ነው። አስተሳሰባችን ውስጥ ድህነት ካለ በኢኮኖሚ አ...
    Disponible

    18,76 €