Librería Samer Atenea
Kálamo Books
Librería Elías (Asturias)
Librería Kolima (Madrid)
Librería Proteo (Málaga)
ይህ መጽሓፍ፥ በኣንድ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከምዕራባዉያን በተለይ ከተባበሩት መንግስታት ኣሜሪካ ልኣላውነቱን የሚጋፋ ተጽእኖ በሚወርድበት ባለው ባሁኑ ሰኣት፥ በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ህዝብ ላለፉት 20 ዓመታት በተባበሩት መንግስታት ኣሜሪካና ምዕራባውያን ኣገሮች ይወርድበት የነበረውን ጫናና ፍትሃዊ ያልሆነ የጸጥታው ምክር ቤትን ማዕቀብ 1907/2009 ተቛቑሞ ልኣላውነቱንና ነጻነቱን በማያወላውል መንገድ ማረጋገጡን፥ የኢትዮጵያ ህዝብ፥ በተለይ ሊሂቃኑ ተገንዝበው በኣርኣያነት በሚጠቕሱበት ባሉት ባሁኑ ወቅት ለኣንባብያን መቅረቡ፥ ኢትዮጵያውያን በኤርትራ ህዝብና መንግስት ላይ ኣዳብሮውት ባሉት ኣዎንታዊ ንቃተ ህሊና ትንሽ ድርሻ ይኖረዋል ብየ ኣምናሎህ።ይህን መጽሓፍ፥ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኣመራር በኤርትራ ህዝብ የትግል ሂደት ውስጥ ጣልቃ በመግባት ይጠነስሳቸው የነበሩትን ሴራዎችና ያለ ኣቅሙ ይፈጽማቸው የነበሩትን ትንኮሳዎች፥ ህዝባዊ ግንባር፥ በልቦናና በሆደ ሰፊነት ችሎ ባካሄደው ከባድ ጦርነት ነጻነቱን ከመጉናጸፉ ባሻገር፥ ከፍተኛ መስዋእትነት በመክፈል የኢትዮጵያን ህዝብ ከደርግ ጨቋኝ ስርዓት ነጻ በማውጣት ወሳኝና የኣንበሳ ድርሻ ያበረከተ መሆኑን የሚያጉላ ነአ። ስለ ሆነም፥ በሁለቱም ኣገራት መካከል ለ30 ዓመታት የዘለቀው ጦርነት፥ በኤርትራ ህዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይም ከፍተኛ የሰው እልቂትና የንብረት ውድመት ያስከተለና ታሪኩም በመስተ-ጋብር የተሳሰረ ስለሆነ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያውቀው ይገባል ከሚል እምነት፥ ' ኤርትሮ - ኢትዮጵያ፥ ከመጋረጃው በስተጀርባ' በሚል ርእስ መጽሓፉን ወደ ኣማርኛ ተርጉሜዋሎህ። ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ፥ ከምስረታው ጀምሮ፥ 'ለኤርትራ ነጻነት ዘብ የቆምኩና የተከራከርኩ ነኝ' በማለት፥ የኤርትራውያንን ቀልብ ለማማለል ብዙ ጥሯል። በተለይ ከ 1998 በኋላ፥ በርካታ ኢትዮጵያውያን ይህን ኣባባል ኣምነውት ነበር። ኤርትራ ነጻነቷን ከተጎናጸፈች ከ27 ዓመታት በኋላም ቢሆን፥ ያገሪቱ ምሁራንና ፖለቲከኞች፥ 'ወያኔ ከኤርትራውያን ባላነሰ ለኤርትራ ነጻነት ተሟግቷል' ብለው ጽፍዋል፥ ገናም እየጻፉ ናቸው።ኣንዳርጋቸው ጽጌ፥ በኤርትራ ነጻነት ላይ የማያወላውል ኣቋም እንዳለው በተለያዩ ኣጋጣሚዎች ይገልጽ እንደነበር ባይካድም፥ በነሓሰ ወር 2018 'ያ ረፈረንደም፥ ወያነ ባስቸኳይ በኣንድ ዓመት ውስጥ እንዲካሄድ ባያደርግ ኖሮ፥ የ 5 ዓመት (ጊዜ) gap ኣግኝቶ ቢሆን ኖሮ፥ Normalize በሆነ ሁኔታ ውስጥ ተፈጥሮ ቢሆን ኖሮ፥ የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ካለው ኣጠቃላይ የሆነ ትስስር እንዲህ በቀላሉ 99% የሚሆን ህዝብ ነጻነት ብሎ የማይመረጥበት ሁኔታ ይኖር ነበረ . . .' ይልና፥ በ 2019 ኣጋማሽ ላይም፥ 'ትውልድ እንዳይደናገር እኛም እንናገር' በሚለው መጽ