Librería Samer Atenea
Kálamo Books
Librería Elías (Asturias)
Librería Kolima (Madrid)
Librería Proteo (Málaga)
ቀለም አልባው ፍቅር ( በቤሩት ሰማይ ስር)እሷ ውብ ወጣት ሀበሻዊት ደራሲ ፤ ፍቅርን በድርሰቷ እንጂ በኑሮዋ ቀምሳ የማታውቅ።በድንገት በተፈጠረ አጋጣሚ ከሀገሯ ርቃ ወደ ቤሩት ትሰደዳለች። ነገር ግን በዚያ በአንድ እይታ የጀመረ ፍቅር ልቧን አስጨንቆ መንገድዋን እስከማሳት ድረስ.....እሱ ፣ ማራኪ፣ ኩሩና ባለጸጋ ፈረንሳዊ ወጣት፤ ፍቅርን እንደ ድክመት ቆጥሮ ከስሜት ርቆ የኖረ፣ በቀላሉ የማይደረስበት የሚመስል ።ነገር ግን ዕጣ ፈንታ ሁለቱን ሲያገናኛቸው፣ ፍቅርና ኩራት፣ ስሜትና ፍርሃት፣ ፍላጎትና መሸሽ በአንድ መንገድ ይገናኛሉ።እሷ በገጾቿ ላይ ብቻ የምታውቀውን ፍቅር በእውነት ትኖረው ይሆን? እሱስ ፍቅር ድክመት ሳይሆን ጥንካሬ መሆኑን ይረዳ ይሆን?ቀለም አልባው ፍቅር በፍቅር፣ በኩራት፣ በምስጢር እና በሕይወት ድንገተኛ አቅጣጫዎች መካከል የሚፈተኑ የሁለት ነፍሳት ታሪክ ነው።